በሞሪሺየሱ ውድድር የኢትዮጵያ ታዳጊ አትሌቲክስ ቡድን 3ኛ በመሆን አጠናቀቀ


አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 27 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) በሞሪሺየስ አስተናጋጅነት ሲካሄድ የቆየው 11ኛው የአፍሪካ ታዳጊ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ትናንት ተጠናቀቀ።

በውድድሩ 36 ሃገራት ሲካፈሉ ፥ ከእነዚህ ውስጥ 26 ሃገራት በሜዳልያ ሰንጠረዥ ውስጥ ገብተዋል።

ውድድሩን ናይጀሪያ 9 የወርቅ ፣ 7 የብርና 8 የነሃስ በድምሩ 24 ሜዳልያዎችን በማግኘት በበላይነት ስታጠናቅቅ ፥ ደቡብ አፍሪካ ደግሞ 7 የወርቅ ፣ 9 የብርና 8 የነሃስ በድምሩ በ24 ሜዳልያዎች ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።

ኢትዮጵያ 7 የወርቅ ፣ 7 የብርና 8 የነሃስ በድምሩ 22 ሜዳልያዎችን በማግኘት ውድድሩን 3ኛ በመሆን አጠናቃለች።

ኢትዮጵያ በ2011 በተካሄደ ተመሳሳይ ውድድር 17 ሜዳልያዎችን ያስመዘገበች ሲሆን ፥ የዘንድሮው ውድድር የተሻለ ውጤት የተመዘገበበት ነው።

የናይጀሪያ እና የጋና መገናኛ ብዙሃን ኢትዮጵያ በመካከለኛ ርቀት ያስመዘገብችው ውጤት አበረታች መሆኑን ዘግበዋል።

source fanabc


0 comments :