Ethiopia and world Cup



Goal.com ለናይጄሪያዊያን ማን ቢደርሳችሁ ትመርጣለችሁ ብሎ ባዘጋጀዉ መጠይቅ ላይ ድምፃቸዉን ከሰጡት ዉስጥ እስካሁን 41.9% የሚሆኑት ናይጄሪያዊያን ኢትዮዺያ እንዲደርሳቸዉ ፈልገዋል ይህ ስሜት የተቀሩት ሀገራትም ነዉ ወደ ደቡብ አፍሪካ የአፍሪካ ዋንጫ ከማለፋችን በፊት የጥሎ ማለፋ ድልድል ሲወጣ ብዙዎቹ ኢትዮዺያን ተመኝተዉ ነበር በመጨረሻ ጎረቤታችን ሱዳን እኛን ስታገኘን በካርቱም የነበረዉ ደስታ ልዩ ነበር ጥቅምት 4 ግን ለየላቸዉ..አሁን ደግሞ ትላልቆቹም ሀገራችንን ፈለጉዋት:: የአፍሪካን እግር ኯስ እንዳልመሰረትን በአለም ዋንጫ ማጣሪያ ከእስራኤል ጋር ስንጫወት ፈር ቀዳጅ እንዳልነበርን... ሶስት ግዜ የአፍሪካ ዋንጫን እንዳላዘጋጀን... ዛሬ ግን ታሪክ ተገልብጦ ምትናቅ ሀገር ሆነች...ያለፈዉን ገናና ስሟን ለማስመለስ ከዚህ የተሻለ ትዉልድ ያለ አይመስለኝም...ገናናዋን ኢትዮዺያን..በታሪክ የምናዉቃትን ጠንካራዋን ኢትዮዺያ የምናይበት ቀን ሩቅ አይሆንም..አዋ ትልቅ እንደነበርን ታሪክ ሲነግረን አድገናል ... ደግሞም አይቀርም ትልቅም እንሆናለን:: እጣዉ ሰኞ ይወጣል ቀኑ አይሄድም እንጂ..
Here is my prediction
#Nigeria vs #Ethiopia
#Ghana vs #Burkina_faso
#Senegal vs #Cotedivor
#Algeria vs #Egypt
#Cameroon vs #Tunisia
Source ፍሰሃ ተገኝ

0 comments :